ለቦረናን እንድረስ
ጎበዝ ኢትዮጵያ Facebook ላይ ያለችው አደለችም ብዙዎች ቦርናን ለመርዳት ድርቁ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት 3ዓመታት ህዝቡንም ሆነ የህዝቡ መገለጫ የሁኑትን የሚያረባቸውን እንሰሳቶች ለመርዳት በተቻለው አቅም ከራሱ ቀንሶ ለመርዳት ሲጣጣር ቆይቷል አሁንም መቀጠል አለበት።
ነገር ግን Facebook ላይ ባሉ ጽንፈኞች የተነሳ የቦረናን ጉዳይ ከአደጋነቱ ይልቅ ወደ ፖለቲካ ቁማርነት እየተየረ ነው።ጽንፈኞች ሆነ ብለው ጉዳዩን ወዳልሆነ አቅጣጫ እንዲሄድ በማድረግ አስፈላጊውን እርዳታ እና ድጋፍ የማድረጉን ሂደት እንዲስተጓጎል እያደረጉት ይገኛሉ።
በአንዳንድ የሀገር እና የውጪ ሚዲያውች ሳይቀ ሆነ ተብሎ የድሮ ፎቶዎችን እና ዘገባዎችን በመጠቀም መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዳልሰጠ ለማስመሰል እና ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት በሚያስተዛዝብ አካሄድ እየተጓዙ ነው።
ህዝቡን ለመርዳት የምትፈልጉ ኢትዮጵያዊያን በኦሮሚያ መንግስት የተከፈቱት የእርዳታ ማሰባሰቢያ አካውንቶች
1= ሲንቄ ባንክ 029565101201
2= ንግድ ባንክ 1029565101201
