ከኢትዮጵያዬ ጎን ነኝ!!
በፖለቲካ አመለካከት ልንለያይ እንችላለን!
በውስጥ ችግሮቻችንም አላስፈላጊ እንኪያሰላንቲያና ፍትጊያ ውስጥ ቆይተን ሊሆን ይችላል፡፡
ነገር ግን በእናት ሃገር ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ተለያይቶ አያውቅም! ይህ ፈፅሞ አይከሰትም!!
ማንም እናት ሃገሩን ሌላ እንዲነካበት የሚፈልግና ይህንንም የሚፈቅድ ኢትዮጵያዊ ፤የለም!!!
አዎ ኢትዮጵያዊው የሚለየው ፤መደፈር የሚያንገበግበው በአገሩና በርስት ምድሩ ከመጡበት ፤ደሙ የሚቆጣ፤ ሃሞቱ የሚመር ፤የእግር እሳት የሚሆንበት ቁጣው የሚንተከተክ መደፈርን የማይቀበል እምቢኝ አሻፈረኝ የሚል ፤ያ ነው ኢትዮጵያዊ የሚታወቅበት፤
ኢትዮጵያ ስትነካ ከሰሜን እስከ ደቡብ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ሆ ብሎ ተምሞ የሚነሳ እጅ ለእጅ ተያይዞ ጥቃትን የሚመክት ፤አንተ ቆይ እኔ ልሙት የሚል ፤ክብሩን አሳልፎ የማይሰጥ ቆፍጣና የአባቶቹ ልጅ የትውልድ አደራ ተቀባይ ነው!!
ይህ ነው ኢትዮጵያዊ ከትናንት እስከ ዛሬ ፤ከዛሬ እስከነገ አገሩን አስከብሮ የዘለቀው! ለራሱ የማይሳሳው በመስዋእትነቱ ነፃነትን ለትውልድ ያወረሰው!!
ይህ ነው ኢትዮጵያዊው!!!










