በአዲስ አበባ ከተማ በቀጣዩ ቀናቶች በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል
በዚህ መሰረት አርብ ግንቦት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በሃግቤስ፣ በአዲሱ ሚካኤል፣ በጳውሎስ ሆሰፒታል፣ በሞተራ ሆቴል፣ በጨው በረንዳ፣ በመርካቶ እስከ ሰባተኛ አዲስ ከተማ ት/ቤት፣ በገነሜ ት/ቤት፣ በአትክልት ተራ እና አካባቢዎቻቸው፤
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ፡-
• በራስ ደስታ ሆስፒታል፣ በእየሩሳሌም ሆቴል፣ በሰሜን ቴክኒክ ቢሮ፣ በእምቢልታ ሆቴል፣ በእንቁላል ፋብሪካ፣ በዜና አገልግሎት እና አካባቢዎቻቸው፤
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ፡-
• በራስ ደስታ ሆስፒታል፣ በእየሩሳሌም ሆቴል፣ በሰሜን ቴክኒክ ቢሮ፣ በእምቢልታ ሆቴል፣ በእንቁላል ፋብሪካ፣ በዜና አገልግሎት እና አካባቢዎቻቸው፤
ቅዳሜ ግንቦት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በካዛንቺስ፣ በእንደራሴ ኮንደምኒየም፣ በዮርዳኖስ ሆቴል እና አካባቢዎቻቸው፤
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ፡-
• በጋንዲ ሆስፒታል፣ በለገሀር፣ በጊዮን፣ በብሔራዊ ሆቴል፣ በእስጢፋኖስ፣ በሳልኮስት፣ በስታዲየም፣ ካዛንቺስ በከፊል እና አካባቢዎቻቸው፤
በተመሳሳይ ከጠዋቱ 5፡00 እስከ ምሽቱ 12፡00 ድረስ፡-
• በስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ፣ በግብጽ ኤምባሲ፣ በየካቲት ሆስፒታል፣ በቅድስት ማሪያም ቤተ-ክርስትያን ጀርባ፣ በእሪ በከንቱ፣ በፒያሳ፣ በቀይ ባህር ኮንደሚኒየም፣ በአፍንጮ በር፣ በናይጀርያ ኤምባሲ፣ በችሎት እና አካባቢዎቻቸው፤
እንዲሁም ከምሽቱ 12፡00 እስከ ሌሊቱ 7፡00 ድረስ፡-
• በከጎላጉል ወደ መገናኛ፣ በገቢዎች፣ በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒላል፣ በሻላ መናፈሻ፣ በቦሌ ጤና ጣቢያ፣ መገናኛ በከፊል እና አካባቢዎቻቸው፤
በተጨማሪም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በወይብላ ማሪያም፣ በአንፎ፣ በአውጉስታ፣ በወይራ ሰፈር፣ በወይራ ኮንደሚኒየም፣ በሞቢል፣ በራሺያ ካምፕ፣ በተዘንአ ሆስፒታል እና አካባቢዎቻቸው፤
ሰኞ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በአለም ባንክ፣በአንፎ እና አካባቢዎቻቸው፤
በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
