“የሀገርና የህዝብ ሀብትን ተይዞ የሚሰራበት እንጂ የምናባክነው ሊሆን አይገባም።
Injiner Takele Uma Banti
የሚያባክኑት ላይም ክንዳችን መጠንከር አለበት።በዛሬው እለትም የማአድን ኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ፣ስራውን ያጓተቱና ቃላቸውን ማክበር ያልቻሉ 27 ተቋማት ፈቃድን ሰርዘናል ለ3 ተቋማት ደግሞ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል።
ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ምክንያቶች 67 የኢንቨስትመንት ፈቃዶችን መሰረዛችን ይታወቃል።ይህ ህግና ስርአትን የማስከበር ጉዞ ከህግ ተጠያቂነት ጋር የሚቀጥል ይሆናል።ባለፉት ወራት ከሰራናቸው የፈቃድ ማጣራት ስራዎች በተጨማሪም የማአድን ኤክስፖርትም ትልቁ ትኩረታች ሆኗል።ባለፉት አስር ወራት ከተለያዩ ማአድናት 513.92 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል በተለይ ወርቅ ለሀገራችን የውጪ ምንዛሪ ገቢ አለኝታነቱን እያስመሰከረ ይገኛል።ህግና ስርአትን እያስከበርን የማአድን ዘርፉን በዘመናዊ መልኩ የመገንባት ስራችን የሚጠነክርና እያደገ የሚሄድ ይሆናል።